Back to Archive
Official Publication

የሀረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አሰራሩን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የሚያስችለውን የሶፍትዌር ጥናት ገመገመ

Authorized Byabdi
Release DateMay 12, 2026
የሀረሪ ክልል ማረሚያ  ፖሊስ ኮሚሽን አሰራሩን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የሚያስችለውን የሶፍትዌር ጥናት ገመገመ
የሀረሪ ክልል ማረሚያ  ፖሊስ ኮሚሽን አሰራሩን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የሚያስችለውን የሶፍትዌር ጥናት ገመገመ gallery 1
የሀረሪ ክልል ማረሚያ  ፖሊስ ኮሚሽን አሰራሩን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የሚያስችለውን የሶፍትዌር ጥናት ገመገመ gallery 2
የሀረሪ ክልል ማረሚያ  ፖሊስ ኮሚሽን አሰራሩን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የሚያስችለውን የሶፍትዌር ጥናት ገመገመ gallery 3

Executive Abstract

"news"

ግንቦት 03/2018 ዓ.ም የሀረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የውስጥ አሰራሩን በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ሥርዓት ለመደገፍ ከሐረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ጋር በጋራ ሲያከናውን የቆየው የሶፍትዌር ጥናት ተጠናቆ ለኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ቀርቧል።

​የጥናት ሰነዱን ለኮሚሽኑ ማኔጅመንት አባላት ያቀረቡት የሐረሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ተወካይ እንደገለጹት፤ ሊበለፅግ የታቀደው ሶፍትዌር የማረሚያ ቤቱን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በዲጂታል መንገድ የሚያስተሳስር ነው።

ሶፍትዌሩ በሁለት ዋና ዋና ምዕራፎች ተከፍሎ እንዲለማ የታቀደ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ የታራሚዎች ምዝገባ፣ የክስ ሂደት፣ የክፍል ድልድልና ሪፖርቶችን ማመንጨት ላይ ትኩረት ያደርጋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ የታራሚዎች የጤና መረጃ፣ የጎብኝዎች ቁጥጥር እና የታራሚዎች የተሀድሶና የሙያ ስልጠና ክትትልን የሚያካትቱ ተጨማሪ ሞጁሎች እንደሚኖሩት በዝርዝር አስረድተዋል።

​በማብራሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የሀረሪ ክልል ማረሚያ ቤቶች ፖሊስ ኮሚሽነር አድናን አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ተቋሙ ያለውን መረጃ አያያዝ ዘመናዊና የተቀላጠፈ ለማድረግ እንዲህ ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል።

​ኮሚሽነር አድናን አክለውም "ይህ የሶፍትዌር ጥናት የማረሚያ ቤቱን የፍትህ ስራ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው ከማድረጉም ባለፈ፣ የታራሚዎችን መረጃ በአግባቡ ለመያዝ እና የተሀድሶ ስራችንን በውጤት ለመለካት ትልቅ አቅም ይፈጥራል" በማለት የጥናቱ መጠናቀቅ ለቀጣይ ስራዎች መሳካት መሰረት መሆኑን ጠቁመዋል።

​በመጨረሻም የጥናት ሰነዱ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ የኮሚሽኑ ማኔጅመንት አባላት ሶፍትዌሩ ወደ ተግባር በሚገባበት ወቅት ሊሟሉ ስለሚገባቸው መሰረተ ልማቶችና የሰው ሃይል ስልጠናዎች ላይ ሃሳብ ሰጥተውበታል።

Authenticated Document Archive

© 2026 Harari Prison Police Commission • All Rights Reserved